የአማራ ህዝብ ትግልን ለመቀልበስ በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ቤተመንግስቱን ከተቆጣጠረው አካል በቀጥታ ወደ አማራ ክልል እየተላከ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
በአማራ ክልል ትጥቅ አስፈታለሁ ብሎ የሞከረው የሰው በላው ስርአት መሪ አብይ አህመድ አሁን ላይ የሚሆነውና የሚሰራው ነገር ጠፍቶበታል ይላሉ ምንጮቹ።
በተደጋጋሚ የአማራ ህዝባዊ ሃይል ትግልን ለማኮላሸት ቄስ፣ ሼክና ታዋቂ ባለሃብቶችን ያሰማራው ይሄው ቡድን ሊሳካለት አልቻለም ብለዋል።
ስለዚህ አሁን ላይ በዋናነት እንደ አጀንዳ ተደርጎ የተቀመጠው አጭበርባሪ ባለሐብቶችን በመጠቀም በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብን ወደ ክልሉ እንዲወስዱና ህዝባዊ ሃይሉን እንዲደልሉ ማድረግ መሆኑንም ያነገራሉ።
ይሄ ገንዝብ ተጭኖ እየተላከ ያለው ደግሞ በመከላከያ ተሽከርካሪዎች መሆኑንም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
ነገር ግን ይላሉ አሁን ላይ ህዝባዊ ሃይሉን ለማታለል የሚላከው ገንዘብ ህጋዊ ያልሆነና የሰው በላው ስርአት መሪ አብይ አህመድ በህገወጥ መንገድ ያሳተመው መሆኑን በግልጽ ሊታወቅ ይገባል ሲሉም አስምረውብታል።
ለዚህ ደግሞ በዋናነት የተመረጡት ሆድ አደርና ከአማራ ህዝብ ትግል ጎን ነን በሚል የአማራ ዝህብን እያታለሉ ባሉ የአማራ ባለሃብቶች መሆኑንም ይናገራሉ።
እነዚህ ባለሃብቶች ደግሞ በዋናነት ትእዛዙን የሚቀበሉት በተመስገን ጥሩነህ በኩል መሆኑንም ይናገራሉ።
ለዚህ ማሳያው ደግሞ ደብረወርቅ አካባቢ የሚገኙ የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ላይ የተሰራውን ደባ በማሳያነት ያቀርባሉ።
ከሆድ አደር ባለሃብቶቹ አንዱ በተመሰገን ጥሩነህ ትልእኮ ሰጭነት ከቢቸና ወደ ደብረወርቅ ሲጓዝ የነበረ ጨፍጫፊ ሰራዊት መንገድ ዘግተው ወደ ነበሩ የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ጋር ተልኮ እንደነበር ያነሳሉ።
በዛም ለነበሩት የደበረወርቅ የህዝባዊ ሃይሉ አባላት 500 000 ሽብር ልኮ ከነበራቸው 12 ብሬን 8ቱን ይዘውና ከተላከው ብር 40000 ሺ ብር ብቻ አስቀርተው እንዲጠፉ ማድረጉን ይናገራሉ።
በወቅቱም ወደ 300 የሚሆኑት አባላት ወደገደብና አነገና ትግሉን ትተው እንዱሄዲ ማድረጉን ይናገራሉ።
ይሄ ባለሃብት ብሩን ከመላኩና በዛ ደረጃ ሃይሉን ከመበተኑ በፊት ገንዘብ በመርጨት የተለያዩ ፕሮፓጋንዳዎችን በመስራት ሲከፋፍል መቆየቱንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ከዛም በላይ የመከላከያ አመራርንም ሾፌር ልኮ በደብረወርቅ ትልቅ ግብዣ ማድረጉን ነው ምንጮቹ አስታውሰዋል።
ነገር ግን አሁን ላይ የህዝባዊ ሃይሉን አሰላለፍም ሆነ አቋም ያላወቁት እነዚህ ሆድ አደር ባለሃብቶች ግብር የማይከፍሉና የተሟላና የሂሳብ ሰነድ እንኳን ማቅረብ የማይችሉ የሌባ ስብስቦች መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል ሲሉም ምንጮቹ አጋልጠዋል።
የባለሃብቶቹ እያንዳንዱ ሰነድ በባለስልጣናትና አላግባብ በሆኑ ህገወጥ ስራዎች የተሞላ መሆኑንም ሳይጠቅሱ አላለፉም።
አሁንም ወደ ክልሉ በመከላከያ ተሽከርካሪዎች የተላከው በሚሊየን የሚቆጠር ብር ጉዳይን ህዝባዊ ሃይሉ አስቀሞ ማድረግ ያለበትን ነገር ማሰብ አለበት ሲሉም ምንጮቹ ጠቁመዋል።
תגובות