በጋምቤላ ሰሞኑ የተገደሉት የአማራ ተወላጆች መኖሪያ ቤቶች በእሳት እንዲጋዩ መደረጉን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
የአማራ ተወላጆቹ ከተገደሉ በኋላ ማህበረሰቡ የመጀን ተወላጆች ናችሁ የገደላችኋቸው በሚል ችግሩ መነሳቱን ይናገራሉ።
አሁን ወደ አካባቢው የጸጥታ ሃይል ገብቷል ቢባልም ሁኔታውን ግን በጣም ያሰጋል ሲሉ ነው ሁኔታውን የገለጹት።
በአካባቢው ያለውን ሁኔታ ለማሳየት አንድ ለስራ የሄደ ሹፌር በገጀራ እንዲጨፈጨፍ መደረጉ ነው ይላሉ።
በክልሉ ሶስት ዞኖች አሉ ዞኖቹ ደግሞ በብሔር ነው ስማቸው የተሰየመው ሲሉ በብሔር ለይቶ የመጨረሽን አጀንዳ ያነሳሉ።
አማራውም ሆነ የመጀን ሰዎች በጋራ አብረው መሬታቸውን ሲያርሱ እንደኖሩ ያነሳሉ።
አሁን ግን የተነሳው ነገር ከጀርባው አንድ የተደበቀ ነገር አለው የሚሉት ነዋሪዎቹ ምሽቱን ተገለው ያደሩት የአማራ ተወላጆች መኖሪያ ቤቶች እንዲቃጠሉ መደረጉ በራሱ ሌላ አጠያያቂ ነገር ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
Comments