top of page

ሰኔ 1/2015በምስራቅ ጉጂ ዞን መብታቸውን ለመጠየቅ አደባባይ በወጡ ሰልፈኞች ላይ የኦህዴዱ መከላከያ ሃይል ከባድ ድብደባ መፈጸሙን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360

ሰኔ 1/2015

በምስራቅ ጉጂ ዞን ከባድ ድብደባ መፈጸሙን ነዋሪዎቹ ገለጹ።



በምስራቅ ጉጂ ዞን መብታቸውን ለመጠየቅ አደባባይ በወጡ ሰልፈኞች ላይ የኦህዴዱ መከላከያ ሃይል ከባድ ድብደባ መፈጸሙን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።



የጉጂ ማህበረሰብ በተደጋጋሚና በተለያየ ጊዜ እየተደረገ ያለው ነገር ትክክል አለመሆኑን በተደጋጋሚ ለማሳወቅ መሞከሩን ይናገራሉ።



ነገር ግን ለተጠየቀው ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ይሰራ የነበረው ነገር ህዝብን ከህዝብ ማለያየት ነበር ይላሉ።


የህብረተሰቡን የገበያ ቦታ ጨምሮ በአካባቢው የተሰራውን ስራ በመቃወም ለሚመለከተው አካል ደብዳቤ ማስገባታቸውን ሁሉ ይናገራሉ።



ነገር ግን ህብረተሰቡ ይሄንን ጥያቄ ያቅርብ እንጂ የተባለው አካል ጋር የማይዳርስ ሆኖ ሳለ ይሄ አካል ግን ያደረገው ህብረተሰቡ ላይ ጥቃት ማድረስ ነው ብለዋል።



የመከላከያውም ሆነ የአካባቢው ፖሊስ በንጹሃን ዜጎች ላይ ይፈጽም የነበረው ድብደባ ህብረተሰቡን እንዳይንቀሳቀስ የሚያደርግ ነበር ይላሉ።



በአካባቢው መጣ የተባለው የኦህዴዱ አመራርም ችግሩን ከመፍታትና የህብረተሰቡን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ወደ ሃይል እርምጃ ነው የሄደው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።


በአካባቢው በተገኘው የኦህዴዱ ሃይል በህዝቡ ላይ የደረሰው ጉዳት ከባድ እንደሆነ ገልጸዋል።



ይሄንን ተከትሎም ማህበረሰቡ አደባባይ መውጣቱንም ሳይናገሩ አላለፉም።


ከተፈጸመው ድብደባ ጋር በተያያዘ የሰው ህይወት አይጥፋ እንጂ በርካቶች ግን ተጎድተው ሆስፒታል መግባታቸውን አመልክተዋል።



በንብረት ደረጃም ቢሆን ጉዳቱ ከፍተኛ ነው የሚሉት ነዋሪዎቹ በተለይ የአካባቢው ፖሊስ በማህበረሰቡ ላይ ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።


 
 

Support Us

Donate with PayPal

© 2025 by Ethio360 Media

Connect with Us

  • rumble
  • Telegram
  • TikTok
bottom of page