top of page

ነሀሴ 9/2015የፖለቲከኛው የአቶ ልደቱ አያሌው መኖሪያ ቤት ዛሬ በሰው በላው ስርአት ሃይሎች ሲበረበር መዋሉን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።

ነሀሴ 9/2015

የፖለቲከኛው የአቶ ልደቱ አያሌው መኖሪያ ቤት ዛሬ በሰው በላው ስርአት ሃይሎች ሲበረበር መዋሉን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።


ደብረዘይት የሚገኝው መኖሪያ ቤቱ የተበረበረው በስምንት የፖሊስና የልዩ ሃይል አባላት መበርበሩን ነው ምንጮቹ የሚናገሩት።


ቤቱን ሊበረብሩ የገቡት እነዚሁ ስብስቦች የሚፈልጉትን ማገነት ባለመቻላቸው ለረጅም ሰአት በቤቱ ውስጥ መቆየታቸውንም ሳይጠቁ አላለፉም።


ቤቱን ሲበረብር ከነበረው ቡድን መካከል የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ልብስን የለበሱ እንደነበሩበትም ምንጮቹ ይናገራሉ።


ከጠዋቱ አራት ሰአት አካባቢ በተደረገው በዚሁ ብርበራ ሁለት የአይን እማኞች ናቸው የተባሉ ግለሰቦችም አብረው እንደነበሩ ጠቁመዋል።


ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ይዘን መተናል ያለው ይሄውን ስብስብ ለቤቱ ጥበቃ ግን ማዛዣውን እንዲያነብ አልፈቀደለትም ብለዋል።


ፈታሽ ነኝ የሚለው ቡድን ለረጅም ሰአት ቤቱ ውስጥ ሲበረብር ጊዜውን ቢያጠፋም ከቤቱ ውስጥ ያገኘው ምንም ነገር ባለመኖሩ ባዶ እጁን ተመልሷል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ተናግረዋል።


 
 

Support Us

Donate with PayPal

© 2025 by Ethio360 Media

Connect with Us

  • rumble
  • Telegram
  • TikTok
bottom of page