top of page

ኢትዮ 360 - ነሀሴ 4/2015) የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና በወሰዱ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመው ግፍ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊጋለጥ ይገባል።

  • Aug 10, 2023
  • 1 min read


በ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና በወሰዱ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመው ግፍ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊጋለጥ የገባል ሲሉ የኢትዮ ምንጮች ገለጸዋል።


ወንዶች በከባድ ተደብድበዋል፣ሴቶች ተደፍረዋል፣ በፍተሻ ሰበብ ቤተሰብ የሰጣቸው ገንዘብ ሰው በላው ስርአት ባሰማራው ሃይል እንዲሰርቁ ተደርገዋል ይላሉ።


ኢትዮ 360 በቅርቡ ባወጣው መረጃም የተረጃ ልጆች በሚል ተለይተው እንዲፈተኑ ለተደረጉት ተማሪዎች አንድ አስተማሪ ተመድቦ ለጥያቄዎቹ መልስ ሲሰጥ መቆየቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።


በአንጻሩ ደግሞ ለብዙሃኑ ተማሪ ሶስት ፈታኞችን መድቦ የነበረው አካል በነዚሁ ተመደቡ በተባሉት መምህራን አማካኝነት ተማሪዎች እንዲፈሩ ሲደረጉ፣ሲረበሹ ሰአታቸውን ሳይጨርሱ ፈተና ሲነጠቁ መቆየታቸውንም ኢትዮ 360 በመረጃዊ ሲያጋልጥ ቆይቷል።


በቃሊቲ አካባቢ ለፈተና የተመደቡ ተማሪዎች ላይ የደረሰው ግን ሊናገሩትና ሊሰሙት የሚከብድ ነው ሲሉም ምንጮቹ ይናገራሉ።


በቅርቡ ኢትዮ 360 ያናገራቸው የተፈታኝ ተማሪዎች ወላጆች ይሄንን ግፍ የፈጸመው ብርሃኑ ነጋ በአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ይቅረብልን ሲሉ መጠየቃቸው ይታወሳል።


 
 

Support Us

Donate with PayPal

© 2025 by Ethio360 Media

Connect with Us

  • rumble
  • Telegram
  • TikTok
bottom of page