ግንቦት 23/2015 በሰሜን ሸዋ መንዝና አካባቢው በኦህዴዱ የመከላከያ ሃይል መወረሩን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
- Ethio 360 Media 2

- Jun 1, 2023
- 1 min read
በሰሜን ሸዋ መንዝና አካባቢው በኦህዴዱ የመከላከያ ሃይል መወረሩን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ወደ አካባቢው የገባው ይሄው ሃይል ደግሞ ሞላሌ አካባቢ ቆሎ ማርገፊያ በሚባል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መመሸጉን ይናገራሉ።
ተማሪዎቹም ሆኑ መምህራኑ ጦር መሳሪያ ከያዘ አካል ጋር ሆኖ እንዴት ትምህርት መማር ይቻላል በሚል እምቢተኝነታቸውን ቢገልጹም የወረዳው አመራር ግን ጫና እያደረገባቸው መሆኑን አመልክተዋል።
ይሄ ሃይል ከባድ መሳሪያን ጨምሮ ሌሎች መሳሪያዎችን ይዞ በዛው ትምህርት ቤት መመሸጉን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
መንዝ ላይ እስካሁን ጦርነቱን ባይጀምር አስቀድሞ ግን መንዝ ቀያ ላይ ህዝብን ያነቃሉ የሚባሉ ሰዎችን እያፈነ መሆኑንም ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።







