top of page

ግንቦት 24/2015 የመከላከያ ዘጋቢ ፊልም ይመረቃል በሚል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችና መመህራንን እንዲልኩ ተገደዱ



በአዲስ አበባ ሚኒዬም አዳራሽ ነገ የመከላከያ ዘጋቢ ፊልም ይመረቃል በሚል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችና መመህራንን እንዲልኩ በግዴታ መታዘዛቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።



ከየትምህርት ቤቱ ሰላሳ ተማሪዎችንና አምስት መምህራንን እንዲልኩ በማስጠንቀቂያ ጭምር መመሪያ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።



ይሄ ብቻ ሳይሆን በየትምህርት ቤቱ መዝጋቢ ቡድን ተልኮ ተማሪዎችንና ምምህራንን መዝግቦ መሄዱን ገልጸዋል።


የተመዘገቡት ተማሪዎችም ሆኑ መምህራን የተለያዩ ምክንያቶችን በማስቀመጥ መገኘት እንደማይችሉ ለመግለጽ ቢሞክሩም መቅረት እንደማይችሉ ከማስጠንቀቂያ ጭምር እንደተነገራቸውም አመልክተዋል።



አብይ አህመድና አዳነች ምግብ እያቀረቡ አስምረው ማንም ልቅር የሚል ጥያቄ ማንሳት የለበትም በሚል ማስጠንቀቂያ እንደወረደላቸውም ነው የኢትዮ 360 ምንጮች የገለጹት።

 
 

Support Us

Donate with PayPal

© 2025 by Ethio360 Media

Connect with Us

  • rumble
  • Telegram
  • TikTok
bottom of page